addisTalent - 45 days creator growth challenge
ለጀማሪ ቲክቶከሮች የተዘጋጀ. Launching the Next Generation of Talent.
የ 45 ቀን የቲክቶክ ይዘት ፈጠራ ውድድር። ሁሉም ተወዳዳሪ በ አዲስ አካውንት ከ 0 ይጀምራል። እድል ወይም የቆየ ተከታይ ጥቅም የለውም፤ አሸናፊ የሚያደርገው እውነተኛ ፈጠራ ችሎታ እና ጥረት ብቻ ነው።
- Days
- 45
- Prize Pool
- 70,000 BIRR
Challenge Ends In
Jan 2, 2027, 12:00 AM EAT
Syncing with the challenge clock…
The Podium
70,000 Birr in prizes
- 1st PlaceGrand Prize
40,000Birr
Cash prize
- 2nd Place
20,000Birr
Cash prize
- 3rd Place
10,000Birr
Cash prize
The Manifesto
Two rules. No exceptions.
አዲስ አካውንት
በዚህ ውድድር ላይ ነባር ወይም ተከታዮች ባሏቸው የድሮ አካውንቶች መሳተፍ በፍጹም አይፈቀድም። ውድድሩ ለጀማሪዎች የተዘጋጀ በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ተወዳዳሪ ከዜሮ (0) ተከታይ በአዲስ አካውንት መጀመር አለበት። ይህ ፍትሃዊነቱን ለመጠበቅ ሲባል በምዝገባ ወቅት በጥብቅ ይረጋገጣል።
እውነተኛ እና ንጹህ ስራ ብቻ!
አዲስ ታለንት ለፈጠራ ችሎታ እና ጥረት ዋጋ የሚሰጥ መድረክ ነው። ተከታዮችን በልመና ለማግኘት መሞከር፣ የቦት ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ወይም ጠቃሚ መልዕክት የሌላቸውን ስፓም ቪዲዮዎች መልቀቅ የተከለከለ ነው። እነዚህን አቋራጭ መንገዶች የተጠቀመ አካውንት ወዲያውኑ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል።
FAQ
Questions, answered
የአዲስ ታለንት የ45 ቀናት ውድድር ምንድን ነው?
ይህ ውድድር ጀማሪ የይዘት ፈጣሪዎች (Content Creators) ወደ ዲጂታሉ ዓለም በልበ ሙሉነት እንዲቀላቀሉ ትልቅ መነሻ የሚሆን የዕድገት መድረክ ነው። ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ አዲስ አካውንት በመክፈት የፈጠራ ብቃታቸውን ይፈትናሉ፣ እርስ በርሳቸው ይወዳደራሉ፣ እንዲሁም ማራኪ ቪዲዮዎችን እያቀረቡ የገንዘብ ሽልማት ለማሸነፍ ይፋለማሉ።
የዚህ ውድድር ዋና ዓላማ ምንድን ነው? ውድድሩስ ለማን ነው የተዘጋጀው?
ዋና ዓላማው አዳዲስ ፈጣሪዎች ይዘት የመፍጠርና ታዳሚ የማፍራት ጉዟቸውን በቀላሉ እንዲጀምሩ መደገፍ ነው። ውድድሩ የተዘጋጀው የይዘት ፈጠራ ፍላጎትና ተሰጥኦ እያላቸው እንዴት እና መቼ እንደሚጀምሩ ግራ ለገባቸው ለጀማሪ ፈጣሪዎች ብቻ ነው።
በዚህ ውድድር ላይ በመሳተፌ ምን አተርፋለሁ?
ከገንዘብ ሽልማቱ ባሻገር፣ ውድድሩ የሚያስገኘው ዘላቂ ጥቅም እጅግ የላቀ ነው። ለአሸናፊዎች ከሚወዷቸው ቲክቶከሮች ጋር ተገናኝተው ቪድዮችን እንዲሰሩ ይመቻችላቸዋል። ተሳታፊዎች ሰፊ ታዳሚ (Audience) ያፈራሉ፣ ከሌሎች ፈጣሪዎች ጋር ጠንካራ ትስስር ይፈጥራሉ፣ እንዲሁም ዲጂታል ተፅዕኖን ወደ ገቢ በመቀየር የራስንና የአካባቢን ህይወት የሚለውጡበትን ትልቅ ዕድል ያገኛሉ።
ውድድሩ ለምን በነፃ አልሆነም? ይህ አነስተኛ ክፍያ ለምን አስፈለገ?
ለዚህ ሁለት ዋና ምክንያቶች አሉ፦ 1. ፕሮግራሙን በተሻለ ጥራትና ደረጃ ለማደራጀት የሚወጡትን የጊዜ እና የገንዘብ ወጪዎች በከፊል ለመሸፈን። 2. ለውድድሩ እውነተኛ ፍላጎት ያላቸውን ተወዳዳሪዎች ብቻ ለመለየት ነው። ሁሉም በነፃ የሚመዘገብ ከሆነ የቁጥር መብዛት ስራውን ለማስተዳደር አስቸጋሪ ያደርገዋል።
ነባር ተከታዮች (Followers) ባሉ የድሮ አካውንት መወዳደር እችላለሁ?
በፍጹም አይቻልም። የጨዋታው ሜዳ ለሁሉም ሰው እኩል እና ፍትሃዊ መሆን አለበት። ሁሉም ተሳታፊዎች ከዜሮ (0 ተከታይ) መነሳት ስላለባቸው እያንዳንዱ ተመዝጋቢ በአዲስ አካውንት መጀመሩ በምዝገባ ወቅት በ ይረጋገጣል።
የክፍያ ማረጋገጫ ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል?
ክፍያዎ እንደተፈጸመ መረጃውን በፍጥነት በማጣራት በአጭር ሰዓታት ውስጥ (ከዘገየ እስከ 24 ሰዓት ባለው ጊዜ) ምዝገባዎ ይረጋገጣል። ማረጋገጫው እንደተጠናቀቀ የውድድሩ መግቢያ መልዕክት ይደርስዎታል።
ምዝገባው መቼ ነው የሚዘጋው?
ምዝገባው ውድድሩ ከተጀመረ በኋላ ባሉት የመጀመሪያዎቹ 5 እስከ 10 ቀናት ውስጥ ተጠቃሎ ይዘጋል። የተዝጋቢዎች ቁጥር ከበዛ ግን በማነኛውም ሰአት ምዝገባው ሊቆም ይችላል። የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ቀድመው እንዲመዘገቡ እንመክራለን።
አሸናፊው እንዴት ነው የሚመረጠው?
ውድድሩ ሙሉ በሙሉ ግልፅ እንዲሆን ለአሁኑ ዙር አሸናፊው የሚለየው በ45 ቀናት ውስጥ በለቀቁት ቪዲዮዎች አማካኝነት በቀጥታ ባፈሩት የእውነተኛ ተከታዮች (Followers) ብዛት ላይ ተመስርቶ ነው። ወደፊት በሚመጡት ዙሮች ግን በተለያዩ መለኪያዎች ላይ የተመሰረተ የነጥብ አሰጣጥ ሥርዓት ሊዘረጋ ይችላል።
ማጭበርበር እና አቋራጭ መንገድ በተመለከተ ህጋችን ምን ይላል?
አዲስ ታለንት ለፈጠራ ብቃት እና ጥረት ትልቅ ዋጋ የሚሰጥ ውድድር ነው። ተከታዮችን በልመና ለማግኘት የሚሞክሩ፣ ቦት የሚጠቀሙ ወይም ምንም ጠቃሚ ይዘት የሌለው ስፓም የሚያሰራጩ አካውንቶች በጥብቅ ተገምግመው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋሉ።
ROUND 1 RANKINGS
Stats synced daily at 8:00 PM EAT by the admin team.
Loading rankings…
The live board fills up as soon as contestants are approved and the first daily stats sync lands.
Contestant Dashboard
Track your race
Search your TikTok handle to see your rank, stats and milestones.